ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በስነጥበብ ዘርፍ ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና እና ሽልማት ስነ ስርዓት ዛሬ በእንጦጦ ፓርክ የተካሄደ ሲሆን፣ በትያትር፣ በሙዚቃ፣ ፊልም ጥበብ፣ ስዕል እና ስነ ቅርስ ዘርፍ የረጅም አመታት አስተዋጽኦ ያበረከቱ አንጋፋ ባለሙያዎች ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
“ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች” በሚል መሪ ቃል በእንጦጦ ፖርክ የአንፊ ትያትር የስነ ጥበብ ማዕከል በተከናወነው በዚሁ መርሃ ግብር የዕውቅናና ሽልማት ከተሰጣቸው የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች መካከል አንጋፋዎቹ አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር)፣ አርቲስት ጌትነት እንየው፣ መምህር አቦነህ አሻግሬ፣ አርቲስት አብራር አብዶና ሁለገቧ አርቲስት አሰለፈች አሽኔን ጨምሮ አለማቀፍ የጃዝ ሙዚቃ አቀናባሪና የአፍሪካ ጃዝ አባት በመባል የሚታወቀው ሙላቱ አስታጥቄ ይገኙበታል።