ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ምርት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው ተባለ!

ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ምርት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው ተባለ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናሰሞኑን በሀገሪቱ የተከሰተውን የነዳጅ እጥረት አስመልክተው መግለጫ የሰጡት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋው፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ምርት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ መሆኑን አሳውቀዋል።
“ቀድሞ ይገባ ከነበረው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የነዳጅ ምርት በአሁኑ ሰዓት 3 ሚሊየን ሊትር በቀን ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ይገኛል” ያሉት አቶ እሸቴ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዲፖዎች በቂ ክምችት ያላቸው በመሆኑ በአቅርቦት ላይ ምንም ስጋት እንደሌለ ገልጸው፤ በአዲስ አበባ ዕጥረቱ ያጋጠመውና ረጃጅም ሰልፎች የታዩት አፋር አካባቢ በተፈጠረው “የፀጥታ ችግር” ምከንያት መሆኑንና አሁን ችግሩ በመቀረፉ ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪዎች በብዛት ወደ ሀገር እየገቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY