ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ሩሲያ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ያላቸውን ልዩነት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት አንዲፈታ ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ለቭሮቭ አስታውቀዋል።
ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ግብፅ የገቡት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ለቭሮቭ፣ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በንግድ እና በሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና ከግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሦስትቱን አገራት እንድታደራድር ለሩሲያ ግብዣ ያልቀረበላት ቢሆንም ለዓመታት ከስምምነት ያልደረሰበትን ድርድር ውጤታማ ለማድረግ በአፍሪካ ኅብረት መሪነት ለሚካሄደው ድርድር የሩሲያ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ከግብፅ መሪዎች ጋር የመከሩት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ወደ ኢራን ማቅናታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
በሌላ በኩል፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የመስኖ ውሃ ሃብትና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በቅርቡ ያለስምምነት በተበተነው የሕዳሴ ግድብ ድርድር እና በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብ ላይ አዲስ አበባ ለሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ማብራሪያ መስጠታቸው ተመልክቷል።
“ጥቂት የቡድኑ አባላትና አመራሮችም ተስፋ በመቁረጥ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ሙከራ አድርገው ነበር” ያሉት ሌተናል ጄነራል ባጫ፣ “ይሁን እንጂ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል” ሲሉም ገልፀዋል።