ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– መነሻቸውን ባሕር ዳር በማድረግ፣ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎችን ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ማንኩሳ ከተማ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የገለፀው የዞኑ ፖሊስ መምሪያ፣ በተካሄደው ፍተሻ ከ2 ሺህ 800 በላይ ተተኳሸ ጥይቶች እና 108 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከተያዙት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።