ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የፀጥታ አካላትን ልብስ በመልበስ በመቀሌ ከተማ፣ አይደር ክፍለ ከተማ መንግስታዊ ባልሆነ መጋዘን ውስጥ የተቀመጠ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን እና መድሃኒቶችን ለመዝረፍ ሙከራ ያደረጉ ግለሰቦች በጥበቃ ሰራተኛ ጥቆማ በመከላከያ ሰራዊት እና ፌዴራል ፖሊስ ኃይሎች መያዛቸው ተገልጿል።
የመቀሌ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ኣብርሃ ጎደፋይ “ግለሰቦቹ የተለያዩ መሳሪያዎችን ጩቤ፣ ገጀራ፣ ሽጉጥ ይዘውና የመከላከያ፣ የፌዴራል ፖሊስና ፀጥታ ኃይሎችን ዩኒፎርም አድርገው የመጋዘኑን በር ሰብረው ሲዘርፉና በአይሱዚ ሲጭኑ ተደርሶባቸው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት” ብለዋል።