ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከሳምንታት በፊት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ የተገባላቸው ቃል አለመፈፀሙን ተነገሩ።
“ጠ/ሚ ዐቢይ የኤርትራን ኃይሎች ለማስወጣት፣ በሰብዓዊ ተደራሽነት ላይ እንቅፋቶችን ለማስወገድ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድራሾችን ተጠያቂ ለማድረግ የገቡትን ቃል አለመፈጸማቸው ቅር አሰኝቶኛል” ሲሉ ነው በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ያስታወቁት።
ይህን የፃፉት ከሁለት ቀናት በፊት አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ የፃፉትን መልዕክት ባጋሩበት የትዊተር መልዕክት ላይ ሲሆን፣ ሴናተር ክሪስ በዚሁ የትዊተር መልዕክታቸው “አሁንም በኢትዮጵያ በትግራይ ውስጥ እና ከትግራይ ውጪ የቀጠለው ግፍ ያሳስበበኛል” ብለዋል።