ኢዜማ በአጣዬው ጥቃት የምርጫ ወረዳ አመራር አባሉ መገደላቸውን አስታወቀ!

ኢዜማ በአጣዬው ጥቃት የምርጫ ወረዳ አመራር አባሉ መገደላቸውን አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– “የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአጣዬ በታጣቂ ኃይሎች የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ በደረሰው የሕይወት መጥፋት፣ የዜጎች መፈናቀል እና ንብረት መውደም ሀዘናችንን መግለፃችን ይታወሳል።

የኤፍራታ እና ግድም ምርጫ ወረዳ የኢዜማ ሊቀመንበር የነበረው ስዩም ላቀው በአጣዬ በተፈፀመው ጥቃት ወቅት ሕይወቱ አልፏል።

መኖሪያ ቤቱን እና ድርጅቱን ለኢዜማ ጽሕፈት ቤት በማድረግ የኤፍራታ እና ግድም ምርጫ ወረዳ ኢዜማ ማስተባበሪያ ቢሮ በኃላፊነት ሲመራ የነበረው ስዩም ላቀው ዘረኝነትን አጥብቆ የሚፀየፍ ብቻ ሳይሆን የሚታገል ሀገር እና ወገን ወዳድ በወረዳው ተኪ የማይገኝለት ብርቅ ልጃችን ነበር” የሚለውና “ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ የሐዘን መግለጫ” በሚል ዛሬ የወጣው የፓርቲው መግለጫ “የስዩምን መስዕዋትነት የምንዘክረው በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመገንባት እና የዘር ፖለቲካን ዜግነትን መሰረት ባደረገ ፖለቲካ በመተካት ነው!” ሲል አስታውቋል።

ኢዜማ በአመራር አባሉ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ “ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና ለቅርብ ባልደረቦቹ መፅናናትን እንመኛለን” ብሏል።

LEAVE A REPLY