የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የሀገር ደህንነትን በሚፈታተኑ ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ!

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የሀገር ደህንነትን በሚፈታተኑ ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና ከኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ የተውጣጣው የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል “መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ እያካሄደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ በጽንፈኞቹ የህወሓትና የኦነግ-ሸኔ ቡድኖች እንዲሁም በሌሎች ታጣቂዎች ላይም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል” ብሏል፡፡

ግብረ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ፣ ሀገራዊ ትርምስ ለመፍጠር የተዘጋጁ ሰነዶችና የጥፋቱን ተዋናይ አካላትንም የሚገልፅ መረጃ በደህንነትና በጸጥታ መዋቅሩ እጅ መግባቱን ጠቁሞ “መንግስት ሀገራዊ ህልውናን አደጋ ላይ ለመጣል የሚሞክሩ የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎችን በምንም አይነት ሁኔታ የማይታገስ በመሆኑ ገልጿል።

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱ የፀረ ሰላም ኃይል ታጣቂዎችን እንቅስቃሴ በመረጃ፣ በደህንነትና የፀጥታ መዋቅሩ አማካኝነት በመከታተልና በመቆጣጠር፣ አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል” ሲልም አስታውቋል።

የሀገሪቱን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ፣ እየተወሰደ ያለው መጠነ ሰፊ ህግን የማስከበር እርምጃ ስኬታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ የጥፋት ሀይሎችን ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ጥቆማ በመስጠትና በማጋለጥ እንዲተባበርም የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።  በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ፣

የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው በዚሁ መግለጫ ከተነሱ አንኳር ነጥቦች መካከል:-

*በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት ያየናቸው ግጭቶች፣ የሰላም ማጣትና የደህንነት ስጋቶች በለውጥ ጉዞአችን በእጅጉ ከፈተኑን ፈተናዎች ጎራ የሚመደቡ ናቸው። መንገድ ያስጀመረንን አንድነት ሊደቁሱ፣ እጅ ለእጅ ያስተሳሰረንን ገመድ ሊበጣጥሱ፣ የጋራ ቤታችንን ሊደረማምሱ የሚቋምጡ ብርቱ ፈተናዎቻች ጉዞ ከመጀመራችን በፊትም ነበሩ፣ አሁንም አሉ፤

*መጀመሪያ በውስጣችን ያሉትን ባለሁለት ቢላዋዎች እናጸዳለን፤ ቀን ቀን ለኢትዮጵያ የሚሰሩ የሚመስሉ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ የሚዶሉቱ አሉ፤ እነርሱ ከውጭ ጠላቶቻችን በላይ ዋነኛ ጠላቶቻችን ናቸው፤ አጥር ላይ ተቀምጠው አሸናፊውን አይተው፣ ከተመቻቸው ሊገቡ ካልተመቻቸው ሊሸሹ የሚያስቡ መኖራቸውን አውቀናል፤

*ይህ ወቅት ለኢትዮጵያ ከወሳኝ ወቅቶች አንዱ ነው። በአንድ በኩል ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ምርጫ አድርገን በሕዝብ ድምጽ የሚጸና መንግሥት ለመመሥረት በሂደት ላይ ነን። በሌላ በኩል ደግሞ የሀገራችን ከፍታ አንዱ ማሳያ የሆነውን የሕዳሴውን ግድብ ሁለተኛውን ዙር ሙሌት ለማከናወን እየተጋን ነው። ከእነዚህ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ግሥጋሴ ከሚያሠጋቸው የውጭና የውስጥ ጠላቶች ጋር በየአቅጣጫው ግንባር ለግንባር ገጥመናል።

*በየአቅጣጫው የምናየው የወገኖቻችን አሰቃቂ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ቤትና ንብረት ማውደም፣ ነውጥና ሸፍጥ ሁሉ በሀገር ውስጥ ብቻ የተመረተ አይደለም። አብዛኛው ጥፋት በውጭ ተመርቶ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠም ጥፋት ነው። ግጭቱንና ጥፋቱን ከውጭ አስመጥተው በሀገር ውስጥ የሚገጣጥሙት የእፉኝት ልጆች ናቸው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ የእፉኝቶችን ዋና መፈልፈያ አፍርሰነዋል። ከዚህ በፊት ፈልፍሎ እዚህና እዚያ የጣላቸው ግልገሎቹ ግን አሁንም ይቀራሉ።

*የትኛውንም ዓይነት የብሔርና የእምነት ስም ቢይዙ፤ ከየትኛው የውጭ ኃይል የሚረዱትን ገንዘብና መሣሪያ ቢጨብጡ ኢትዮጵያን ይፈትኗት ይሆናል እንጂ አያሸንፏትም። መጀመሪያ በውስጣችን ያሉትን ባለ ሁለት በላዋዎች እናጸዳለን። ቀን ቀን ለኢትዮጵያ የሚሠሩ የሚመስሉ፤ ሌሊት ሌሊት በኢትዮጵያ ላይ የሚዶልቱ አሉ።

*እነርሱ ከውጭ ጠላቶቻችን በላይ ዋነኞቹ ጠላቶቻችን ናቸው። አጥር ላይ ተቀምጠው፣ አሸናፊውን አይተው፣ ከተመቻቸው ሊገቡ፣ ካልተመቻቸው ሊሸሹ የሚያስቡ መኖራቸውን ዐውቀናል። ወቅቱ የምርጫ ነውና መምረጥ አለብን። ወይ እነርሱን እናጸዳለን ወይ ኢትዮጵያን አሳልፈን እንሰጣለን። የኛ ምርጫ ኢትዮጵያን ለእነርሱ ስንል መሠዋት ሳይሆን፤ እነርሱን ለኢትዮጵያ ስንል መሠዋት ነው። የሚሉት ይገኙበታል።

ብሐራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ ከዚህ በፊት  በሰዎች ላይ ለደረሰው ጥቃትም ሆነ በከተሞች ላይ ለደረሱ ውድመቶች ሀላፊነት አልወሰደም።

LEAVE A REPLY