የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፤ የጸጥታ አካላትና የደህንነት ተቋማትን ወቀሰ!

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፤ የጸጥታ አካላትና የደህንነት ተቋማትን ወቀሰ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “የፀጥታ ኃይሎች የጸጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎች የሚደርሱት ረብሻ ከተነሳና ህይወት ከጠፋ በኋላ ነው። የጸጥታ ሀይሎችና የደህንነት ተቋማት የሰው ህይወት ከጠፋ በኋላ የሚያደርጉት እሳት የማጥፋት ስራ ሊታረም ይገባል” ሲል በመግለጫው አሳስበዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤት ም/ቤቱ በወቅታዊ የሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ ላይ በሰጠው በዚሁ መግለጫው፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት ተቋም ወቅቱን የጠበቀ የቅድመ ማስጠንቀቂያና የሁኔታ ትንተና ለሚመለከተው አካል የማድረስና ከችግሮች ቀድሞ የመገኘት ግዴታና ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቦ፣ በዚህ ላይ ያሳየውን ደካማ እንቅስቃሴ ተችቷል፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባፌ “የመከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ እና ሚሊሻዎችም የጸጥታ ችግር ያለበት ቦታ ላይ የሚደርሱት ህይወት ከጠፋና ረብሻ ከተነሳ በኋላ ነው” በማለት ተችተው አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጸጥታ አካላትም ሆነ የሚመለከታቸው የደህንነት ተቋማት ግዴታና ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ባለመሆናቸው ችግሮች ሊባባሱ መቻላቸውን በመጥቀስ ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል።

LEAVE A REPLY