በቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ የኬንያ፣ የብሪታኒያ፣ የደቡብ አፍሪካና የጃፓን ኩባንያዎች መሳተፋቸው ተገለፀ!

በቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ የኬንያ፣ የብሪታኒያ፣ የደቡብ አፍሪካና የጃፓን ኩባንያዎች መሳተፋቸው ተገለፀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ለሁለት አለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች ፈቃድ ለመስጠት ታስቦ ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም በወጣው ጨረታ ለመሳተፍ ስድስት ካምፓኒዎች ተሣትፈዋል።

ሳፋሪኮም ከኬንያ ፣ቮዳፎን ከብሪታኒያ፣ ቮዳኮም ከከደቡብ አፍሪካ፣ ሲዲሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ፣ ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን እና ኤምቲኤን ግሩፕ ከደቡብ አፍሪካ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በማስገባት መሳተፋቸውን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አሰታወቀ።

ለዓለም አቀፍ ኩባንያዎቹ ፍቃድ ለመስጠት የወጣው የጨረታ ማስገቢያ ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ያስታወቀው፣ ሰነዶቻቸውን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ካስገቡት 6 ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች መካከል አሸናፊ የሚሆኑት ሁለት ድርጅቶች እነማን እንደሆኑ፣ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን በተረከባቸው የጨረታ ሰነዶች ላይ የሚያከናውነውን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ግምገማዎች ካጠናቀቀ በኋላ የሚገለፅ መሆኑ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY