በኢትዮጵያ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ!

በኢትዮጵያ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ራሶ ወረዳ ሀርጌሳ የሬይ በተባለው ቀበሌ እና በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ የደረሱ ሁለት የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።

በሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ራሶ ወረዳ ሀርጌሳ የሬይ በተባለው ቀበሌ ከትናንት በስቲያ ሌሊት በጣለ ከባድ ዝናብ የአራት ህጻናት ህይወት ማለፉንና የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑት አራት ህፃናት ለሞት የተዳረጉት በጎርፍ በመወሰዳቸው መሆኑን የራሶ ወረዳ አስተዳደር ገልጿል።

የ4ቱ ህጻናት አስከሬን በተለያዩ አካባቢዎች መገኘቱን የገለፁት የወረዳው አስተዳዳሪ የህጻናቱ የቀብር ስርዓታቸው በሀርጌሳ የሬይ ቀበሌ ትናንት መፈጸሙን ተናግረዋል።

በሌላም በኩል፣ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ በደረሰ የመሬት መደርመስ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጋጮ ባባ ወረዳ የአደጋ ስጋት አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ዳርጻ አስታውቀዋል።

“በወረዳው ላካ ቀበሌ ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 8 ሠዓት አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ በደረሰ የመሬት ናዳ አደጋ የ1 ወንድ እና የ2 ሴቶች ህይወት አልፏል” ያሉት ኃላፊ አቶ ኢዮብ ዳርጻ፣ በአደጋው ሶስት መኖሪያ ቤቶች ሙሉ መውደማቸውን፣ ስምንት የቤት እንስሳት በአደጋው መሞታቸውንና በ2.5 ሄክታር መሬት የተዘራ ሰብል ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY