“የኢዜማ ሚስጥራዊ የደህንነት ሰነድ” በሚል እየተሰራጨ ስላለው መረጃ ፖርቲው መግለጫ ሰጠ!

“የኢዜማ ሚስጥራዊ የደህንነት ሰነድ” በሚል እየተሰራጨ ስላለው መረጃ ፖርቲው መግለጫ ሰጠ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከትላንት ሚያዚያ 18፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢዜማ ስም በተለያዩ አካላት ሲዘዋወር የዋለ ሰነድ እንዳለ ለመረዳት ችለናል” በማለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ(ኢዜማ) ህዝብ ግንኙነት ከሰአታት በፊት መግለጫ አውጥቷል።

“የኢዜማ ሚስጥራዊ የደህንነት ሰነድ” በሚል ከትናንት ጀምሮ እየሰራጨ ያለው መረጃ ፖርቲውን የማይወክል ስለመሆኑ የገለፀውና “ፍሬ ያለው ዛፍ ድንጋይ ይበዛበታል!” በሚል ርዕስ የወጣው ይኸው የኢዜማ መግለጫ “ከትላንት ጀምሮ በፓርቲያችን ስም እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ ህጋዊ ተቋማትን ጭምር ያሳሳተ በመሆኑ ግልጽ ማድረግ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል ብሏል ኢዜማ።

ሰነዱ ኢዜማን የማይወክል እና ኢዜማ የማያውቀው መሆኑን እየገለጽን ዛሬም እንደትላንቱ ከዛፉ ላይ ፍሬ ይወድቅልናል ያሉ ተስፈኞች የወረወሩት መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን” ብሏል።

“ኢዜማ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያለውን አረዳድ እና የወደፊት ተስፋ በመፅሀፍት አሳትሞ እና ህዝብ እንዲያውቅ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ነው” ያለው መግለጫው፣ ለዚህም ፓርቲው መፅሃፍት ፩ እና ፪፣ የፓርቲውን ፕሮግራምና የዜጎች መድረክ እትሞችን እንዲሁም ምርጫ 2013 የቃልኪዳን ሰነድ በሚሉ ርዕሶች በተለያየ ጊዜ አሳትሞ ያወጣቸውን ማየት እንደሚቻል አስታውቋል።

“በማንኛውም ጊዜ የኢዜማን አቋም ለመረዳት የፓርቲውን ይፋዊ ገፆች እና ህትመቶች ይከታተሉ” ሲልም የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት በመግለጫው አመልክቷል።

LEAVE A REPLY