“ከምርጫ በስተቀር የሚሸጋገር፣ የሚደራደር መንግስት አይፈጠርም” ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

“ከምርጫ በስተቀር የሚሸጋገር፣ የሚደራደር መንግስት አይፈጠርም” ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– “እያንዳንዱ ዜጋ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን አውቆ ዛሬ ጀምሮ ማንን ለምን እንደሚመርጥ እያሰበ ቆይቶ ጊዜ ስላለው ከመረጠ በኋላ ድንጋይ የሚወረውር ከሆነ በጋራ መቆም አለበት” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ደ/ር ዐቢይ አህመድ አሰታወቁ።

“በዚህ ምርጫ ያሻችሁን ምረጡ ግን ሰላም አስቀድሙ፣ በዚህ ምርጫ ያሻችሁን ምረጡ ግን እኩል መድረክ መፈጠሩን አረጋግጡ” ብለዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ከምርጫ በስተቀር የሚሸጋገር፣ የሚደራደር መንግስት አይፈጠርም። ማንም ሰው ስልጣን መያዝ የሚችለው በምርጫ ብቻ ነው፤ ይህን አውቆ የሚፎካካር ሀይል ሀሳብ ካለው፣ አደረጃጀት ካለው ሐሳቡን ሸጦ፣ ህዝብ አሳምኖ እንዲመረጥ፤ እኛ ደግሞ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የምንፈልግ ሀይሎች በተቻለ መጠን አውዱ ለዚህ የሚመች መሆኑን አውቀን በመስራት ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ የስልጣን ሽግግር እና ቅቡል መንግስት መፍጠር ይጠበቅብናል” በለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “ዲሞክራሲ አብቦ እንዲያፈራ፣ ተፎካካሪዎችም፣ ህዝብም፣ መንግስትም በከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት መስራት ይኖርብናል፡፡ ኢትዮጵያን አሸናፊ የሚያደርግ ምርጫ ሰላማዊ፣ ለሁሉም የሚፎካከሩ ሀይሎች እኩል መድረክ የፈጠረ፣ በሐሳብ የላቀ፣ በተግባር የበቃ፣ በልምድ የተሳካ፣ ቃል ለመግባት ሳይሆን ሰርቶ ለማሳየት የቆረጠ፣ ህዝቡን የሚያዳምጥ፣ ህዝቡን የሚያከብር፣ የማይሰርቅ ሀይል ስልጣን የሚይዝበት ምርጫ እንዲሆን እንፈልጋለን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ  “ከዚህ ውጪ ያሉ ሐሳቦች ሁሉ ቅዠቶች ናቸው። የጀመርነውን ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ያደናቅፍ ይሆናል እንጂ አይሳካም” ብለዋል፡፡

 

LEAVE A REPLY