አቶ ልደቱ አያሌው ለህክምና ከሀገር ወጡ!

አቶ ልደቱ አያሌው ለህክምና ከሀገር ወጡ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በተደጋጋሚ በመንግስት ደህንነቶች ከሀገር እንዳይወጡ እግድ ሲደረግባቸው እና ከኤርፖርት እንዲመለሱ ሲደረጉ የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው ትላንት ምሽት ከሀገር መውጣታቸው ታውቋል።

አቶ ልደቱ አያሌው ህክምናቸውን ለመከታተል ወደ አሜሪካ ሀገር የሄዱ ሲሆን፣ ከሀገር ሳይወጡ በፊት ከኤርፖርት ሆነው ባሰራጩት የእጅ ፅሁፋቸው መልዕክት “አሁን የይለፍ ቁጥጥር ክፍሉን አልፌ ወደመሳፈሪያ ክፍሉ ገብቻለሁ።

ዛሬ ጉዞዬ የሚሳካ ይመስላል። ባሳለፍኩት ውጣ ውረድ ከጎኔ ለቆማችሁ የፍትህ ወዳጄች በሙሉ ምስጋናዬ እጅግ ከፍተኛ እና ልባዊ መሆኑን በአክብሮት እገልፃለሁ። ጤናዬ ተስተካክሎ በሰላም እንደምመለስ እና ምስጋናዬን በድጋሜ ለማቅረብ ዕድል እንደማገኝ ተስፋ አለኝ። ሰላም ለውዷ አገራችን!” ብለዋል።

ከትላንት በስቲያ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ከሀገር እንዳይወጡ በፖሊስ የተላለፈውንና በፍርድ ቤት ጸንቶ የነበረውን እግድ ስለመሻሩ መዘገባችን ይታወሳል።

LEAVE A REPLY