ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በየአመቱ የዩኒቨርስቲዎችን ዓመታዊ ደረጃ የሚያወጣውና US News Global የተሰኘው የአሜሪካ ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን “የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚው ምርጥ ዩኒቨርሲቲ ብሎታል።
US News Global ዘንድሮ ባወጣው የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ከ80 በላይ በሚሆኑ አገራት የሚገኙ 1 ሺህ 500 ዩኒቨርስቲዎችን በውድድሩ እንዳሳተፈ የገለፀ ሲሆን፣ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከአፍሪካ 10ኛ እና ከዓለም 553ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል።
በዘንድሮ የተቋሙ ደረጃ የአሜሪካው ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ከዓለም ቀዳሚ ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዟል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ዓመት በዚሁ ተቋም በተሰጠ ደረጃ ከምስራቅ አፍሪካ 2ኛ ከዓለም ደግሞ 616ኛ ደረጃን አግኝቶ ነበር።