ሱዳን “ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእኔ ነው ማለቷ አስነዋሪ ነው” ተባለ! || ፕ/ት...

ሱዳን “ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእኔ ነው ማለቷ አስነዋሪ ነው” ተባለ! || ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደሱዳን አቀኑ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ “የሱዳን ባለስልጣናት የህዳሴ ግድባችን የሚገኝበትን የቤኒሻንጉል አካባቢ በተመለከተ የእኛ ነው የሚል መረጃ መልቀቃቸው አስነዋሪ ነው” ሲሉ ተችተውታል።

“የሱዳን ወታደሮች ድንበር አልፈው የኢትዮጽያን አርሶአደሮች ማፈናቀላቸው ሳያንስ እንዲህ አይነት መረን የወጣ መረጃ መልቀቃቸው የሚኮነን ነው። የኢትዮጵያ መንግስትም ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል” ያሉት አምባሳደር ዲና “ሱዳኖች የሚያወጡት መግለጫ ያለአግባብ የተለጠጠ እና አለም አቀፍ ህግጋትንም ያላከበረ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ጥዋት ሱዳን መግባታቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ በሱዳን የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል።

በፕሬዝዳንቱ በሚመራው ልዑክ ውስጥ፣ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳሌህ እና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ እንደሚገኙበት የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

LEAVE A REPLY