ኢትዮጵያ ባለፈው አመት 7 ጋዜጠኞችን እንዳሰረች አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቡድን አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ባለፈው አመት 7 ጋዜጠኞችን እንዳሰረች አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቡድን አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናዓለም አቀፉ የፕሬስ ነፃነት ቀን በዓለም ለ30ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ “መረጃ ለህዝብ ጥቅም” በሚል ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በፓናል ውይይት ተከብሯል።

በፓናል ውይይቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በኢትዮጵያ የዩኔስኮ ተወካይ ዶክተር ዮሚኮ ዮኮዜኮ “ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ በፕሬስ ነፃነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ በማሳየት 51 ደረጃዎችን ያሻሻለች ቢሆንም የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት እየተፈታተናት ይገኛል” በማለት የሀሰተኛ መረጃዎች ሥርጭት የከፋ ደረጃ ላይ እንዳይደርስ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛ መረጃ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እንድሪስ በበኩላቸው “በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛ መረጃ በመስጠት አገርና ህዝብን ሊጠቅሙ ይገባል” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆች አመት 7 ጋዜጠኞችን እንዳሰረች አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቡድን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

“አብዛኞቹ ታሳሪ ጋዜጠኞች በጸረ መንግሥት ወንጀል እንደተከሰሱ የጠቀሰው ቡድኑ፣ ፖሊስ የጋዜጠኞቹን እስር እያራዘመ መቆየቱን አመልክቶ “ሆኖም መንግሥት ባሰራቸው ጋዜጠኞች ላይ አንዳችም ማስረጃ አላቀረበም” ብሏል። ሪፖርቱ አያይዞም፣ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ኢንተርኔት ለረጅም ጊዜ በሚዘጋበት እና የትግራዩ ጦርነት ጥላ ባጠላበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለመስራት እንደተገደዱ ገልጿል።

LEAVE A REPLY