ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ፣ ከቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል የኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል መረጃ በመጠየቅ እና ሐሰተኛ ምላሽ በመስጠት ስራ ላይ የተሰማራ የወንጀለኞች ቡድን መኖሩን አስታውቋል።
ዝርዝር ጉዳዮችን ያልዳሰሰውና “ህብረተሰቡ ሐሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ” የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤቱ አጭር ማሳሰቢያ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
“የወንጀለኞች ቡድን ከቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል የኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል መረጃ በመጠየቅ እና ሐሰተኛ ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸውን ዐውቀናል።
በመሆኑም ሁሉም ሰው ሐሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና ጥፋት የሚያስከትሉ እንቅስቃሴዎችን ለሕግ አስከባሪ አካላት እንዲያሳውቅ እናሳስባለን።