ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢፌዴሪ አየር ኃይል በትግራይ ክልል በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጀብድ ለፈጸሙና በተቋማዊ ሪፎርም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ከፍተኛ መኮንኖች ዛሬ የማዕረግ እድገትና እውቅና ሰጥቷል፡፡
የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “በአሁኑ ወቅት ከውጭና ከውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሀገሪቱን ለማፍረስ እየሠሩ ቢሆንም ዓላማቸው አይሳካም” በማለት፣ ጠላቶችን ለመመከትም አየር ኃይሉ በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል
በዛሬው የማዕረግ እድገትና እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር፣ 44 ከፍተኛ መኮንኖች፣ 47 መስመራዊ መኮንኖች እና 985 ባለማዕረግ የአየር ኃይሉ አባላት፣ በድምሩ 1079 የተፈቀደላቸውን ማዕረግ ተቀብለዋል፡፡