የእነ ስብሃት ነጋ ክስ የምስክሮች ስምና አድራሻ ሳይጠቀስ በዝግ ችሎት እንዲታይ ተወሰነ!

የእነ ስብሃት ነጋ ክስ የምስክሮች ስምና አድራሻ ሳይጠቀስ በዝግ ችሎት እንዲታይ ተወሰነ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የእነ ስብሃት ነጋን የክስ መዝገብ እያየ የሚገኘው የፌደራል አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ የቅድመ ምርመራ ሂደቱ በዝግ ችሎት እና የምስክሮች ስምና አድራሻቸው ሳይጠቀስ እንዲቀጥል ዛሬ ውሳኔ አስተላልፏል።

ዐቃቤ ህግ “ለምስክሮች ጥበቃ አድርጌአለሁ” ማለቱን መነሻ በማድረግና በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን መቃወሚያ ከመረመረ በኋላ ውሳኔውን መስጠቱን የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ፣ በዐቃቤ ህግ በኩል የተነሳው የምስክሮች ጥበቃ ህገ-መንግስታዊ መሆኑን ገልጾ፣ ፍርድ ቤቱ ከቀረቡለት ሶስት የምስክር አሰማም ሂደቶች ሁለቱን መቀበሉንም አመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን በሰጠበት ዝርዝር ሰነድ እንደገለፀው፣ ተቀባይነት ካገኙት የምስክር አሰማም ሂደቶች የመጀመሪያው ማንኛውም ሚዲያ እና ታዳሚ ሳይገባ በዝግ ችሎት የቅድመ ምርመራ ምስክሮች የሚሰሙበት ሲሆን፣ የምስክሮች ስም እና አድራሻ ለተጠርጣሪዎች ሳይጠቀስ የምስክሮች ቃል የሚሰማበት ሁለተኛው አካሄድም ተቀባይነት አግኝቷል።

በአንፃሩ፣ የምስክር አሰማም ሂደት፤ ምስክሮች በአካል ሳይታዩ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዲመሰክሩ በሚል በዐቃቤ ህግ የቀረበውን ሃሳብ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል።

LEAVE A REPLY