የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሊያገረሽ እንደሚችል አስጠነቀቀ

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሊያገረሽ እንደሚችል አስጠነቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ አዳዲስ የቫይረሱ ዝርያዎች መገኘታቸው፣ የክትባት አቅርቦቶች መዘግየት እና የህብረተሰቡ የጥንቃቄ መጠን መቀነስ ቫይረሱ በድጋሚ ሊያገረሽ እንደሚችል ማሳያዎች ናቸው ብሏል፡፡

በህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የኮቪደ 19 ዝርያ በአንድ የአፍሪካ አገር መገኘቱንና ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ የተገኘው ዝርያ ደግሞ በሌሎች 23 የአፍሪካ አገራት መታየቱን ያስታወቀው ድርጅቱ፣ የተወሰኑ የአፍሪካ አገራት ክትባቶችን በማከፋፈል ረገድ አበረታች እንቅስቃሴ እያሳዩ እንደሆነና እስካሁን አህጉሪቱ ከተቀበለችው 37 ሚሊዮን ክትባቶች ውስጥ የተወሰዱት ግማሾቹ ብቻ መሆናቸውንም አመልክቷል።

LEAVE A REPLY