ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– “አል-ቡርሃን ስልጣናቸውን በቅርቡ ሊለቁ ይችላሉ፤ ከዛ በፊትም የሱዳን ሲቪሉ ክንፍ ቁልፍ ተቋማትን በመቆጣጠር ላይ ነው” ሲሉ ከሱዳን የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል።
የሱዳኑ የፖለቲካ ተንታኝ መሐመድ ዴኪን “ሱዳን በአሁኑ ወቅት በተለይም በባለስልጣናት ደረጃ ፈጣንና ተጨባጭ ልውጦቶችን እያስተናገደች ነው። የሽግግር መንግስቱ ሲቪል ወገን በንቃት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ወሳኝ በሆኑ ተቋማት ላይ የበላይነትን ለመያዝና ለማጥበቅ እየሰራ ይገኛል” ብሏል።
ባለፉት ጥቂት ቀናትም የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች በሱዳን መንግስት ሁለት ወገኖች መካከል ስላለው ልዩነት በስፋት ማተት መጀመራቸው ወታደራዊው የአል-ቡርሃን አገዛዝ በቅርቡ ሊበተን እንደሚችል አመላካች ነው ተብሏል።