የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትናንት ለተፈጠረው “የአደባባይ ኢፍጣር” መስተጓጎል ይቅርታ ጠየቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትናንት ለተፈጠረው “የአደባባይ ኢፍጣር” መስተጓጎል ይቅርታ ጠየቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትናንት ለተፈጠረው የአደባባይ የኢፍጣር መርሐ ግብር መስተጓጎል በምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አማካኝነት ይቅርታ ጠይቋል።

“ረመዳን ከሪም!” በሚል መልካም ምኞት ዛሬ የተላለፈው የምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የይቅርታ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል:-

ውድ የከተማችን ሙስሊም ወገኖቻችን፣ የኢትዮጵያ አደባባዮች የሁሉም ኢትዮጵያዊን ናቸው! አብሮ አንድ ማዕድ በጋራ የተቋደሰ ፤ አደባባይ “የኔ፣ ያንተ” ብሎ አይጣላም፡፡ ትላንት በጎዳናዎች ላይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የአፍጥር ስነስርአት ተስተጓጉሏል።

ይህ የሆነው ወቅታዊ የደህንነት እና የጸጥታ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የቦታው ስፋት እና ርዝመት ውስን እንዲሆን ባቀረብነው ሀሳብ አዘጋጅ ኮሚቴው ባለማመኑ ብቻ መሆኑ ግልጽ እንዲሆን እንፈልጋለን ።
የትላንት ምሽት ሁኔታ የሁላችንም ሰላም እና ደህንነት እንዲጠበቅ አስፈላጊ ጥንቃቄ ለማድረግ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ለማድረግ ብቻ የተንቀሳቀሱት እንጂ በፍፁም የአፍጥር ክልከላ አይደለም ።

በተለያዩ የከተማ አካባቢዎች የአፍጥር ስነስርዓት መካሄዱን አይተናል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ይህን ጉዳይ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለመውሰድ በማህበራዊ ሚዲያ ሊያራግቡት ሞክረዋል።
በዚህ

ሁኔታ ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰማውን ቅሬታ የገለጸበት መንገድ ጨዋነት የተሞላበት እና ሰላማዊ መሆኑ ሊደነቅ ይገባል። ትላንት ለተፈጠረው ነገር በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ።
በድጋሜ ረመዳን ከሪም!

LEAVE A REPLY