ልዩ መልዕክተኛው “አሜሪካ በኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በትብብር እንደምትሰራ ማረጋገጣቸው” ተገለጸ!

ልዩ መልዕክተኛው “አሜሪካ በኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በትብብር እንደምትሰራ ማረጋገጣቸው” ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ አሜሪካ በኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በትብብር እንደምትሰራ የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ጄፈሪ ፊልትማን አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፈሪ ፊልትማን ከተለያዩ የፌዴራል መንግሥት ኃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አደርገዋል።

ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በነበራቸው ውይይት፣ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በትብብር እንደምትሰራ ማረጋገጣቸውን የገለፁት ቃል አቀባዩ፣ ጄፈሪ ፊልትማን ኢትዮጵያ የአሜሪካ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗንና አሜሪካ በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች በተጠናከረ መልኩ ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንደምትፈልግ መግለጻቸውንም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

አገራቸው አሜሪካ በህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በሚሳተፉት አገራት መካከል ሰላማዊ መፍትሄ ያለው ውጤት እንዲመዘገብ የበኩሏን እገዛ እንደምታደርግ መናገራቸውን እንዲሁም በመጪው ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ፣ በትግራይ ክልል ስለሚከናወን የሰብዓዊ ድጋፍ እና የሱዳን ድንበር ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉንም አምባሳደር ዲና
ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY