ኢትዮጵያ ለኬንያ ልትሸጥ ያሰበችው የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ዝርጋታ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ለኬንያ ልትሸጥ ያሰበችው የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ዝርጋታ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ ከጊቤ ሶስት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከሚመነጨው ኃይል 400 ሜጋ ዋት ኃይል ለመሸጥ ወደ ኬኒያ የኃይል ማስተላለፊያ ጣቢያና የማስተላለፊያ መሥመር ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት የኢትዮ-ኬንያ ፓወር ሲስተም ኢንተርኮኔክሽን ፕሮጀክት ሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ አያሌው፣ በኢትዮጵያ በኩል በወላይታ ሶዶ ከተማ የጣቢያው ግንባታና 446 ኪሎ ሜትር መሥመር ዝርጋታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ ቴዎድሮስ፣ ከኬንያ ወገንም ተመሳሳይ የኃይል ማስተላለፊያ ጣቢያ በሱስዋ ከተማ ሆኖ የ600 ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መሥመር ዝርጋታ እየተከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬሽን ፕላኒንግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲኣ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አፍሪካን በኃይል በማስተሳሰር አንድ የኢኮኖሚ ቀጠና ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በማገዝ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል።

LEAVE A REPLY