ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አንጋፋው የታሪክ ምሁር አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ “የአማራ ደም የእኔም ደም ነው ብለሃል፣ የመንግስት ግልበጣ ለማድረግም ስታሴር ተደርሶብሃል” የሚል ክስ በአቃቤ ህግ እንደቀረበባቸው ተሰምቷል።
አቶ ታዲዮስ “የሽግግር መንግስት ለማቋቋም መክረሃል” የሚል ክስ እንደቀረበባቸው፣ ትናንት በዋለው ችሎት የ15 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው፣ ከባለቤታቸው በስተቀር ሌላ ሰው እንዳይጠይቃቸው የተከለከሉት ስለመሆኑና ለግንቦት
13/2013 ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት እንደሚቀርቡ መቀጠራቸውን ባለቤታቸው ወይዘሮ ፀጋ ሞገስ
ተናግረዋል።