ቅዱስ ፓትርያርኩ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎመውን “ቃለ ዐዋዲ” ዛሬ በይፋ መረቁ!

ቅዱስ ፓትርያርኩ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎመውን “ቃለ ዐዋዲ” ዛሬ በይፋ መረቁ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትመራበት ቃለ ዐዋዲ በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ አማካኝነት በእንግሊዘኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዛሬ ተመርቋል።

በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተከናወነው የቃለ ዐዋዲው ምረቃ ስነስርዓት ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰበካ ጉባዔ ማደራጃና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁአን አበው ሊነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY