በህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እየኾነ መምጣቱን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ!

በህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እየኾነ መምጣቱን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እየኾነ በመምጣቱ፣ ማኅበረሰቡ የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን በጥንቃቄ እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ መግለጹን የተቀሰው ኢንስቲትዩቱ፣ ቫይረሱ እስካሁን በ44 ሀገራት እንደተሰራጨ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመልክቷል፡፡

“ቫይረሱ አሁንም የጤና ስጋት በመሆኑ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የመከላከያ መንገዶችን በጥንቃቄ እንዲተገብር” ሲልም የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል፡፡

በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደዘገቡት፣ በአሁኑ ሰዓት በህንድ የሰው ልጆች እንደቅጠል እየረገፉ ሲሆን፣ ሆስፒታሎች ሞልተዋል፤ የኦክሲጅን እጥረትም አጋጥሟል። ባለፉት አምስት ቀናት ብቻም ህንድ ውስጥ 19,952 ሰዎች ሲሞቱ፣ 1,750,209 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

LEAVE A REPLY