በሙዚቀኛው ኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል!

በሙዚቀኛው ኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡የተወዳጁን ሙዚቀኛ የኤልያስ መልካን ኪናዊና ግላዊ ሕይወት ከተለያዩ ንድፈ ሀሳቦች አንፃር በስፋት የመረመረ “የከተማው መናኝ” የተሰኘና 409 ገጾች ያሉት አዲስ መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ እንደሚመረቅ ተገልጿል።

የጥናታዊ መጽሐፉ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው እንዳለው፣ የከተማው መናኝ በሚል ርዕሥ ለገበያ ለመብቃት የተዘጋጀው መጽሐፍ የአንድ ብዙ የሆነውን አቀናባሪውን፣ ጊታር ተጫዋቹን፣ ግጥምና ዜማ ደራሲውን እንዲሁም ፕሮዲውሰሩን ኤልያስ መልካን ከፍልስፍና፣ ከነገረ-መለኮት፣ ከሳይንስ፣ ከታሪክና ኪነ-ጥበብ ሃልዮት አንፃር በስፋት ለመፈተሸ የሞከረ ስራ ነው፡፡

“ኤልያስ መልካ የቅርብ ሩቅ የሆነ ባለሙያ ነበረ” ያለው ጸሐፊው፣ አዲሱ መጽሐፍ የኤልያስ አድናቂዎች የሚያነሷቸውና ለማወቅ የሚጓጉላቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ መመሞከሩን አብራርቷል፡፡

“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ፣ ነገ ቅዳሜ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለኤልያስ ክብር በሚዘጋጀው ታላቅ ዝግጅት እንደሚመረቅም ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው ከኢትዮጵያ ነገ ዘጋቢ ጋር በነበረው አጭር ቆይታ ገልጿል።

ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እና ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ፣ ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ጋር በተያያዙ መሰናዶዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ በተለያዩ የሕትመት ውጤቶች ላይም ሰፋ ያሉ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትንታኔዎች በማቅረብ ይታወቃል፡፡

LEAVE A REPLY