ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ፖለቲከኛው እስክንድር ነጋ የፃፈው “ድል ለዴሞክራሲ” የተሰኘ አዲስ መፅሃፍ ገበያ ላይ መዋሉ ተሰምቷል።
እስክንድር ነጋ በቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ፣ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የፃፋቸው ፅሁፎች ስብስብ በአንድ ጥራዝ በመፅሐፍ መዘጋጀታቸውን በይፋዊ ፌስቡክ ገጿ የገለፀች ባለቤቱ ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል፣ መፅሀፉ ከትናንት አርብ ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በገበያ ላይ እንደሚውል አስታውቃ “አካሉን እንጂ ሃሳቡን አታስረውም ብለን ነበር፤
ድል ለዲሞክራሲ” ስትልም መልዕክቷን አስተላልፋለች።