ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል የልዑክ ኃላፊ ዢ ቲያን ቻይና በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚካሄደውን የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ አሰተወቀቸ።
ዢ ቲያን የመንግስታቸውን አቋም ባስታወቁበት መልዕክታቸው “ቻይና እንደ አንድ የአፍሪካ ወዳጅ አገር ግድቡ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ትረዳለች። በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት ግድቡን በተመለከተ የሚካሄደውን የሦስትዮሽ ድርድርም ትደግፋለች” ብለዋል።
ቻይና የአፍሪካ አገራት ወዳጅ እንደመሆኗ ግድቡ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው እንረዳለን፤ በተለይም ደግሞ ለኢትዮጵያ ልማት ያለውን ጠቀሜታ እናውቃለን” ብለዋል።
“በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት ግድቡን በተመለከተ የሚካሄደው ድርድር በውይይት መፍትሄ ለማምጣት ለሚደረገው ጥረት ትክክለኛ መንገድ ነው፤ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርህም እንደግፋለን። ከማለታቸውም በተጨማሪ አገራችን ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የአፍሪካ ኅብረት ከሚያካሂደው ድርድር እንዳይወጡና ልዩነቱን በውይይት እንዲፈታ ታበረታታለች” ሲሉም
ዢ ቲያን የመንግስታቸውን አቋም ተናግረዋል።