5 የመንግስት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ!

5 የመንግስት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ!

– ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ደህንነት የሚጠብቁ አጃቢዎች ተመረቁ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየምዕራብ ወለጋ ዞን ጸጥታ ቢሮ የቀድሞ ኃላፊን ጨምሮ አምስት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።

የቀድሞው የጸጥታ ቢሮ ኃላፊው አቶ ዋቅጋሪ ቀጄላና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ከቆንዳላ ወረዳ ወደ መንዲ ለሥራ ጉዳይ በመጓዝ ላይ ሳሉ በታጣቂዎች መገደላቸውን የገለፁት የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ “ጥቃቱን ያደረሱት ራሳቸውን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብለው የሚጠሩትና በቅርቡ መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጃቸው የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ የአለም አቀፍ ተቋማትን ዲፕሎቶችንና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ደህንነት የመጠበቅ (VIP Protection) ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ 104 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትናንት ተመርቀዋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ለተመራቂዎች የስራ መመሪያ የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ፣
ተመራቂቹ የወሰዱትን የክህሎት፣ የአቅም ግንባታ በተግባርና በንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ስልጠና በልብ በታመነ አገልጋይነት በተግባራዊ የስራ እንቅስቃሴ ሊተገብሩት እንደሚገባ አሳስበዋል።

 

LEAVE A REPLY