ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከ55 ሺህ በላይ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ያፈሩት፣ የዘብር ገብርኤል ደብር አሁን ላለው እውቅና ግዙፍ መንፈሳዊ ትሩፋት ያበረከቱትና በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ላሎ ወረዳ የሚገኘው ዘብር ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ለ50 ዓመታት ሲያስተዳድሩ የቆዩት መላከ ምህረት ቆሞስ አባ የኔታ አክሊሉ ወልደማርም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።
የ107 ዓመት የእድሜ ባለጸጋው የኔታ አባት አክሊሉ በአካባቢውም ይሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው መንፈሳዊ አባት የነበሩ ሲሆን፣ ሥርዓተ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት፣ በመንዝ ላሎ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መፈጸሙን ከወረዳው መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡