ኮሮናን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ በተላለፉ 1200 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ!

ኮሮናን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ በተላለፉ 1200 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ፣ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ በተላለፉ አንድ ሺህ 2 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ፡፡

ከግንቦት 2 እስከ 10/2013 ዓ.ም ብቻ ትርፍ በመጫን 603፣ ማስክ አለማድረግ 204፣ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል 91፣ መስመር አለመሸፈን 65፣ ታፔላ አለመስቀል 38 እና በስራ ሰዓት መቆም 1፣ በድምሩ 1 ሺህ 2 አሽከርካሪዎች መመሪያ ጥሰው በመገኘታቸው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ቢሮው ገልጿል።

በመመሪያው መሰረት፣ ትርፍ በመጫን መተላለፍ፣ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ የኮቪድ 19 መከላከያ ተግባራት አለማከናወን፣ በስራ ሰዓት ያለ ሥራ ቆሞ መገኘት እና ታፔላ ሳይሰቅል መስራት ከ5 መቶ እስከ 2 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ መደንገጉ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY