ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ መወሰኑን ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ገለጹ!

ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ መወሰኑን ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ገለጹ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አዲስ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ፣ የሚኒስትሮች ም/ቤት መወሰኑን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፃቸው ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት “የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታሪካዊ ውሳኔን ወስኗል። ከፍተኛ የፈቃድ ክፍያ ዋጋ እና አስተማማኝ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት ዕቅድ ላቀረበው ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አዲስ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ በአንድ ድምፅ አጽድቋል” በማለት የገለፁ ሲሆን፣ አያይዘውም “በአጠቃላዩ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በሚበልጥ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት፣ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ከተደረጉት የውጪ ቀጥተኛ የሙዓለ ነዋይ ፍሰቶች ብልጫ እንዲኖረው ያደርገዋል። ኢትዮጵያን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት የማስገባት ዕቅዳችን ፈር ይዟል። ይህንን ግልጽነት እና ውጤታማነት የሞላበት ሂደት ላሳካችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ” ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ፣ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተው ከትናንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ “የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዛሬ ጠዋት በተደረገ ውይይት አዲሱን የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ ሂደት በዝርዝር አቅርቧል። ይህም ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር የተቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ተከናውኗል” በማለት ገልፀው የነበረ ሲሆን፣ የሚኒስትሮች ምክር ዛሬ ውሳኔውን ያስተላለፈው አማካሪ ምክር ቤቱ ባቀረበው ዝርዝር ላይ ተወያይቶ መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል።

 

LEAVE A REPLY