ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመጪው የክረምት እርሻ ወቅት መጀመር በፊት ለመመለስና በዘለቄታውም ለማቋቋም በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ውይይት ተደረገ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተመራ፣ ከፍተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሁለቱ ክልሎች ባለሀብቶች፣ ምሁራን እና የእምነት ሰዎች የተገኙበት ምክክር መደረጉን የጠቀሱት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ፣ ይህን በጎ ጅምር በማስፋት በክልሎቹ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ምክክሩ በሁለቱ ህዝቦች መካከል በቀጣይ በስፋት ለሚተገበሩ የመግባቢያ የውይይት መድረኮችና የሰላም ግንባታ ሒደቶች ብሎም የመልሶ ማቋቋም ስራ በር ከፋች የሆነ በጎ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
መላው የአገራችን ህዝብ ይህንን የሰላምና የህዝባዊ ግንኙነት ማበልፀጊያ ጅምር በንቃት በመከታተልና በመደገፍ ለዜጎቻችን ያላችሁን አጋርነት እንድታሳዩ በትህትና እማፀናለሁ” ሲሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጥሪ አስተላልፈዋል።