አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ዓለም አቀፋዊ ውግዘት እየገጠመው ነው!

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ዓለም አቀፋዊ ውግዘት እየገጠመው ነው!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ በማቅረብ እና አካባቢውን ለረጅ ድርጅቶች ክፍት አድርጎ ሳለ የአሜሪካ ውሳኔ ግን የራሷን የጥቅም ፍላጎት የማሳከት ዓላማን የያዘ ነው።

አሜሪካ ምክንያት አድርጋ ያቀረበችው በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አልደረሰም የሚለው ሀሰት ነው፤ በአሁኑ ወቅት ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ ሆኖ ሳለ እንዳልተደረገ መጠየቋ ዓላማዋ የሌላ ጥቅም እና ፍላጎት አንጂ ማዕቀብ ለመጣል በቂ ምክንያት አይደለም” ብለዋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ እገዳ የኢትዮጵያን እና የአሜሪካን የ120 ዓመታት ዲፕሎማሲ ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ኢትዮጵያም ግንኙነቷን እንደምታጤነው ተናግረዋል።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከአልሸባብ ዘመቻ በፊት እንኳን በኮሪያ ዘመቻ ከአፍሪካ በብቸኝነት የአሜሪካ አጋር ሆና የነበረችው ኢትዮጵያ በመሆኗ ግንኙነቱ ሲበላሽ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አሜሪካም ተጎጅ እንደምትሆን የገለፁት ቃል አቀባዩ “አሜሪካ የወሰነችውን ውሳኔ ታጢነው። እኛ ያለን ግንኙነት እንዲቋረጥ አንፈልግም። በምንም መልኩ ግን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ እንዲነካ አትፈቅድም” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ብሪታንያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ቶም ፋውዲ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ተከትሎ ባሰራጨው ፅሁፍ “አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ አንዲሁም ከፊል የኢኮኖሚ ማእቀብ መጣሏ፣ በቻይና ባለሀብቶች የተያዘውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ወደ አሜሪካ በመውሰድ የመንግስት የኢኮኖሚ አቅምን እርዳታ በመከልከል ለማዳከም፣ አንዲሁም በአሜሪካ የፖለቲካውን አሰላለፍ የሚደግፉ ካምፓኒዎችን በኢትዮጵያ በመሰግሰግ ሀያልነቷን ለማሳየት ነው” ብሏል።

“ሰሞኑን በወጣው የኢትዮ ቴሎኮም ጨረታ በአሜሪካው ኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት ኮርፖሬሽን ብድር የሚቀርብለት ነገር ግን ከቻይናው ዜድቲኢ እና ሁዋዌ ምንም አይነት እቃ የማይገዛው ወይም እቃ እንዳይጠቀም በኮርፖሬሽኑ ስምምነት የገባው የቮዳፎን፣ ቮዳኮም፣ ሳፋሪኮምና ሱሚቶሞ ጥምረት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የቻይናን ኢንቨስትመንት ለመቀነስ አልማ አንደተነሳች ያሳያል። ከጨረታው ውጤት ማግስት በትግራይ ጦርነት ሰበብ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ በከፊል እርዳታ መቀነሷ፣ መንግስትን በኢኮኖሚ አዳክሞ በመንግስት እጅ ያሉትን ትላልቅ ድርጅቶችን ለግል ባለሀብቶች አዛውሮ በዚህም አሜሪካ ተጠቃሚ ሆና በሀገሪቱ ላይ ትልቅ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተፅእኖ ማሳደር በመቻል መንግስትን አንደፈለገች ማሽከርከር አንድትችል በማሰብ ነው። ይሄ ደግሞ ለኢትዮጵያ ለመንግስት ምቾት አይሰጥም። አይኑንም ሙሉ በሙሉ በቅድሚያ ወደ ቻይና ቀጥሎም ወደ ራሺያ ሊያዞረው ይችላል።

ያ ማለት ደግሞ አሜሪካ የሶማሊያውን አማፂ ቡድን አልሻባብን በመዋጋት አጋር የሆነቻትን ለቀይ ባህር እና ለህንድ ውቅያኖስ ቅርብ የሆነችውን ስትራቴጂክ አጋሯን ኢትዮጵያ ማጣት ይሆንባታል” ሲልም ብሪታንያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ቶም ፋውዲ በሲጂቲኤን እና በአርቲ ሚዲያ ትናንት ባሰራጨው ፅሁፉ አመልክቷል።

LEAVE A REPLY