በኢትዮጵያ “ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ ነገ ይካሄዳል!

በኢትዮጵያ “ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ ነገ ይካሄዳል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና የሚያሳድሩትን ጫና በመቃወም “ድምፃችን ለነፃነታችን ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል፣ ወጣቶችን ያሳተፈ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነገ በመላው ኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የሰልፍ መርኃ ግብሩ ነገ እሑድ ግንቦት 22/2013 በተመሳሳይ ሰአት በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን መሆኑንና በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች እንደሚሳተፉበት የገለፀው የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ “የአሜሪካ መንግስት ከሰሞኑ የጣለው የቪዛ ክልከላና በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረው ጫና ሀገሪቱ ከድህነት እንዳትላቀቅ ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ለሀገር እድገት የበኩላቸውን በመወጣት የውጭ ጫናን መቃወም ይገባቸዋል” ብሏል።

ይህ ወቅት ህዝቡ ይበልጥ አንድነቱን ሊያጠናክርበት እንጂ ህብረ ብሔራዊነቱን ሊያደበዝዝ እንደማይገባ የገለፀው ኮሚቴው፣ ከምዕራባውያን ጫና ለመላቀቅ መስራትና በትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባም አመልክቷል

በተያያዘ፣ የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ለነገው ሰልፍ ሰላማዊነት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

“ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄደው የወጣቶች ንቅናቄ መድረክ፣ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

“ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ልዩ ልዩ የአደባባይ ኩነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ በትዕግስት፣ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በመደጋገፍ ላሳየው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ኮሚሽን ምስጋናውን እያቀረበ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ተገንዝበው ለፍተሻ እንዲተባበሩ” ሲልም ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

LEAVE A REPLY