የኢትዮጵያ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ከ68 ዓመት በላይ ሊሻሻል መሆኑ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ከ68 ዓመት በላይ ሊሻሻል መሆኑ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ክፍያ ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እንደገለጹት፣ ከ68 ዓመታት በላይ በስራ ላይ የቆየውን የኢትዮጵያ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ለማሻሻል የሚያስችል አዲስ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የዳኝነት የክፍያ ደንብ ፍርድ ቤቶች ለሚሰጡት አገልግሎት ተመጣጣኝ ገቢ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን በውይይቱ ላይ የጠቀሱት ወ/ሮ መዓዛ “ክፍያው ወቅቱን ያላገናዘበ በመሆኑ አገልግሎቱን ለማሻሻል፣ መሰረተ ልማቱን ለመገንባትና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ እንዳያድግ አድርጓልም” ብለዋል።

አሁን የተሻሻለው ረቂቅ ደንብ የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅምና ወቅታዊ የዋጋ ግሽበትን ባገናዘበ መልኩ መሆኑን ያመለከቱት ፕሬዝዳንቷ፣ የቀደመው የአገልግሎት ክፍያ ደንብ ከፍርድ ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ ለመውሰድ ሃምሳ ሳንቲም እንደሚጠይቅ፣ ይህ ክፍያ በአሁኑ ወቅት ያለውን የአንድ የወረቀት ሂሳብ እንኳን የማይሸፍን መሆኑንና ለፍርድ ቤቶች እየመጡ ያሉ ጉዳዮች ውስብስብና ሰፊ በመሆናቸው ይህንን መሸፈን የሚያስችል ገቢም ስለሚያስፈልግ የማሻሻያ ረቂቁ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ ለውይይት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ታክሎበት በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብም ፕሬዝዳንቷ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY