በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 473 ሺህ ዶላር፣ 393 ሺህ ዩሮ እና...

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 473 ሺህ ዶላር፣ 393 ሺህ ዩሮ እና 39 ሺህ ፓውንድ ተያዘ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናመነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሞያሌ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 473 ሺህ 770 ዶላር፣ 393 ሺህ 660 ዩሮ እና 39 ሺህ 675 ፓውንድ፣ ኮድ 2 አ.አ B 67186 በሆነ ፒካፕ መኪና ውስጥ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የሻሸመኔ ፖሊስ መምሪያ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ አድርጎ ባደረገው ክትትል የተያዘው ህገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ፣ ወደ ኢትዮጵያ ሲመነዘር 44 ሚሊየን ብር ግምት እንዳለው የገለጸው ፖሊስ፣ ገንዘቡ የተያዘው በሻሸመኔ ከተማ 05 ቀበሌ በተለምዶ ሞቢል በሚባለው አካባቢ መሆኑንና በተሽከርካሪው የውስጠኛው አካል በረቀቅ መንገድ ተደብቆ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ባደረገው ጥብቅ ፍተሻ የፋብሪካው ብሎን ተከፍቶ የተደበቀው ገንዘብ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ሊያዝ መቻሉን ገልጿል።

LEAVE A REPLY