ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ!

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ፣ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣና ለዚህም ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ አስታውቀዋል።

ከምርጫው በተጨማሪም፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት እንዲከናወን እና በመላው ሀገሪቱ ወንጀለኛን አድኖ ለመያዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑን የተናገሩት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ “ምርጫው በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY