የመጀመሪያው ኢስላሚክ ባንክ ስራ ጀምረ! የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ አንደሚችሉ ተጠቆመ!

የመጀመሪያው ኢስላሚክ ባንክ ስራ ጀምረ! የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ አንደሚችሉ ተጠቆመ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ዘምዘም ኢስላሚክ ባንክ፣ ስራ ያስጀመረውን አሊፍ ቅርንጫፍ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በቦታው ተገኝተው ዛሬ ስራ አስጀምረዋል።

ብሔራዊ ባንክ ለኢስላሚክ ባንክ መቋቋም መስመር ከከፈተ በኋላ ስድስት አዲስ ባንኮች ስራ የመጀመር እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ የኢስላሚክ ባንክን ስራ ያስጀመረ ሊሆን መብቃቱ በተነገረበት የዛሬው ምረቃ ስነስርዓ፣ 11,000 ሰዎች የባንኩን አክሲዮን መግዛታቸው፣ እንዲሁም ከወለድ ነፃ አገልግሎትና ሌሎች የኢስላሚክ ባንክ አገልግሎቶችን ለመስጠት ታቅዶ የተከፈተው ባንክ በአመት ውስጥ ከ50 በላይ ቅርንጫፎችን ለመክፈት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ መች እንደሆነ ባይታወቅም የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ አንደሚችሉ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ጠቁመዋል።

በአሊፍ ቅርንጫፍ ተገኝተው የዘምዘም ኢስላሚክ ባንክን ዛሬ ስራ ያስጀመሩት ዶ/ር ይናገር፣ በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮችም አቅማቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY