ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአሜሪካ ፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሚሊየነርና የ”US Doctors For Africa” መስራች የሆኑት ቴድ አለማየሁ፣ “የኢኮኖሚ ማዕቀቡ በእሳት ላይ በቤንዚል እንደመጨመር ነው።
ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ በማደግ ላይ ያሉ አንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራትን ይጎዳል። የጆ ባይደን አስተዳደር ከዚህ አደገኛ መንገድ ይልቅ ብዙ ነገሩን የሚፈቱ መፍትሄዎች ላይ አተኩሮና ሃላፊነት ወስዶ መስራት አለበት” ሲሉ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፃቸው ይሄን አመልክተዋል።
በአሜሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ናቸው ከሚባሉ ባለሀብቶችና የፖለቲካ ሰዎች መካከል ከግንባር ቀደሞቹ ጋር የሚጠቀሱት ቴድ አለማየሁ፣ በዚሁ የፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት አስተያየታቸው “በአቶ መለስ ዜናዊ ጊዜም ተቃዋሚ ቡድኖች ሀገሪቱ ላይ ማዕቀብ ይደረግ ሲሉ ተዉ አይሆንም፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ብዙ ደሃዋችን ይጎዳል ብዬ ተከራክሬያለው” በማለት አሜሪካ በቅርቡ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተቃውመዋል።