የእስክንድር ነጋ አዲስ መፅሃፍ ነገ ይመረቃል! እስረኞቹ የባልደራስ አመራሮች የምርጫ ሰርተፊኬት ተቀበሉ!

የእስክንድር ነጋ አዲስ መፅሃፍ ነገ ይመረቃል! እስረኞቹ የባልደራስ አመራሮች የምርጫ ሰርተፊኬት ተቀበሉ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ፖለቲከኛው እስክንድር ነጋ የፃፈው “ድል ለዴሞክራሲ” የተሰኘ አዲስ መፅሃፍ፣ በአዲስ አበባ ራስ አምባ ሆቴል በሚከናወን በልዩ ዝግጅት ነገ ይመረቃል።

በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር፣ እስክንድር ነጋ በቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ የፃፋቸው ፅሁፎች ስብስብ፣ በአንድ ጥራዝ መፅሐፍ ተዘጋጅቶ “ድል ለዴሞክራሲ” በሚል ርዕስ ከሁለት ሳምንት በፊት ለንባብ ስለመብቃቱ ባለቤቱ ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲልን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ አመራሮች የምርጫ ተወዳዳሪነት ስተፍኬታቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

አመራሮቹ በ6ኛው ሐገራዊ ምርጫ፣ በምርጫ ተወዳዳሪነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከምርጫ ቦርድ የተሰጣቸው መሆኑንና ፓርቲው ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ከምርጫ ቦርድ የዕጩነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጠው ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም መጠየቁን የገለጹት የፓርቲው የሕግና ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ፣ ሰነዱን በአንድ ቀን እንደሚያስረክብ በችሎት ፊት ቃሉን የሰጠው ምርጫ ቦርድም ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም የዕጩነት ማረጋገጫ ሰነዱን ለፓርቲው ማስረከቡን አረጋግጠዋል።

ይሁንና፣ ከሳምንት በፊት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩም፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ በመጪው ምርጫ በዕጩነት እንዲመዘገቡ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መስጠቱን ተከትሎ፣ ፓርቲው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርግ” ሲል ላቀረበው ጥያቄ፣ ቦርዱ በሰጠው ምላሽ “…የእጬዎች ምዝገባ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በመጠናቀቁ፤ እንዲሁም እያንዳንዱ እጩ ተወዳዳሪዎች በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረውን ስፍራ የሚወስን ሎተሪ እጣ በመውጣቱና፤ በዚሁ መሰረት የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመትም ተጠናቆ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የመላኩ ተግባር በቅርብ ጊዜ የሚጀመር በመሆኑ፤ እንደውሳኔው ለመፈፀም ቦርዱ የሚቸገር መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን” በማለት በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ አመራሮች በምርጫው መሳተፍ የሚችሉበት ዕድል እንደሌለ መግለፁና ይህንኑም በዝርዝር መዘገባችን ይታወሳል።

LEAVE A REPLY