ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የፓርላማ ዘመን፣ 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛና 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን፣ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ፣ የቀረቡትን አጀንዳዎች መርምሮ በሙሉ ድምፅ ካፀደቀ በኋላም በአጀንዳዎቹ ላይ መምከር መጀመሩ ታውቋል።
ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው፣ የቀረቡ ቃለ ጉባኤዎችን መርምሮ በሙሉ ድምጽ ካጸደቀ በኋላ “በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል” ተብለው በቀረቡት ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔ እንደሚያሳልፍም ከየፌዴሬሽን ምክር ቤት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡