የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች “ለዓመታት ተፈጽሞብናል ያሉትን ግፍና በደል” በአደባባይ ሲያስተጋቡ ዋሉ!!

የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች “ለዓመታት ተፈጽሞብናል ያሉትን ግፍና በደል” በአደባባይ ሲያስተጋቡ ዋሉ!!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ባዕከር ከተማ ነዋሪዎች፣ “አሸባሪው ትህነግ ለዓመታት ሲፈጽምብን ኖሯል ያሉትን ግፍና በደል” እንዲሁም የውጭ ኃይሎችን ጫና በመቃወም የአደባባይ ሰልፍ አካሂደዋል።

“ብዙዎች ሰምተው እንዳልሰሙ፣ ዓይተው እንዳላዩ ዝምታን መርጠው ኖረዋል። በግፍ ውስጥ ዓመታትን ያሳለፍነው ነዋሪዎች ግን ከጥያቄያችንና ከትግላችን አልቆምንም። በፅናት የቆምንለት ትግል ፍሬ አፍርቶ ከአሸባሪው ትህነግ አገዛዝ ነፃ ወጥተናል” ያሉት ነዋሪዎቹ፣ ለዓመታት በጭቆና ውስጥ ሳሉ “የት ናችሁ?” ያላሉ ሁሉ ከነፃነታቸው ማግሥት ሀሳብ መስጠት መጀመራቸውን አውስተው “በተለይም አሜሪካ በወልቃይት ጠገዴ የተገኘውን ነፃነት የማይመጥን ሀሳብ እያራመደች በመሆኑ ከዓመታት የግፍ አገዛዝ ነፃ የወጣን ነዋሪዎችም የአሜሪካን እና አጋሮቿን ጫና በመቃወም አደባባይ ወጥተናል” ብለዋል።

“በማንነትና በሉዓላዊነት ከማንም ጋር አንደራርም፣ አሸባሪው ትህነግ የፈፀመብን ግፍና በደል ይታወቅልን፣ የ30 ዓመታት ግፍና በደላችንን ዓለም እንዲያውቅልን እንፈልጋለን፣ በማንነታችን እና በርስታችን አንደራደርም፣ አሸባሪው ትህነግ ይመለሳል ብላችሁ የምትጠባበቁ ከዳተኞች ተስፋችሁን ቁረጡ፣ በአማራ ላይ ለተፈጸመው የግፍ ጥግ ማሳያ ወልቃይት ጠገዴ ነው፣ ባለፉት 30 ዓመታት ብዙ ማይካድራዎችን አይተናል፣ ወደ ኋላ ላንመለስ ነፃ ወጥተናል” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አንግበው አደባባይ መውጣታቸውንም ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

ለ60 የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ሰነዶች አለመታተማቸውና ለ54 የምርጫ ክልሎች የታተሙት ጉድለቶች እንደተገኘባቸው ተገለጸ!

60 ለሚሆኑ የምርጫ ክልሎች መታተም የነበረባቸው የድምጽ መስጫ ሰነዶች በአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂ ችግር ምክንያት አለመታተማቸውንና ለ54 የምርጫ ክልሎች የታተሙ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ጉድለቶች እንደተገኘባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ትናንት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ያጋጠመው ችግሮችን ለመፍታት አማራጭ የሕትመት ሥራዎች በአፋጣኝ ተሠርተው ምርጫው በተቆረጠለት የጊዜ ሰሌዳ ሰኔ 14 እንደሚካሄድ ገልጸው፣ ችግሩ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በአይ.ሲ.ቲ ለማዘመን በሚሠራው አድካሚ ሥራ ላይ የተፈጠረ እንደሆነ እና መንስኤውም ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም፣ የዕጩዎችን ቁጥር መሰረት አድርጎ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ወቅት ፓርቲዎች የዕጩዎች ቁጥር ላይ ባቀረቡት አቤቱታ፣ በድምፅ መስጫ ወረቀት እና በውጤት ማሳወቂያ ፎርሞች ላይ የማስታረቅ ሥራ ሲሰራ ለ54 የምርጫ ክልሎች በታተሙ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ላይ ጉድለቶች መገኘታቸውን ያመለከቱት ዋና ሰብሳቢዋ “ቦርዱ ባደረገው ማጣራት ጉድለት የተገኘባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ አስታውቀዋል።

በአፋር 6፣ በአማራ 11፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ 2፣ በጋምቤላ 3፣ በኦሮሚያ 2፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች 15፣ በሶማሌ 14 እና በድሬዳዋ 1 የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ምርጫ ክልሎች መሆናቸውም በዋና ሰብሳቢዋ ተመልክቷል።

LEAVE A REPLY