ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አወዛጋቢነቱ የቀጠለው መስቀል አደባባይና ከለገሐር እስከ ማዘጋጃ ቤት ድረስ የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ነገ በይፋ እንደሚመረቁ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ፕሮጀክቶች ነገ ሰኔ 6/2013 ዓ.ም እንደሚመረቁ አረጋግጦ በዕለቱ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።
እንደ ፖሊስ ኮሚሽኑ መግለጫ ከሆነም የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦
– ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ
– ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ
– ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ
– አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
– ጎላ ሚካኤል
– ጥቁር አንበሳ ሼል
– ሜትሮሎጂ
– ጎማ ቁጠባ
– ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ
– ለገሃር ጉምሩክ መብራት
– ቡናና ሻይ
– ገነት መብራት
– 4ኛ ክፍለ ጦር (ጥላሁን አደባባይ)
– ቂርቆስ መታጠፊያ
– አጎና ሲኒማ
– ኦሎምፒያ
– ኡራኤል አደባባይ
– ባምቢስ መታጠፊያ
– ካዛንቺስ ሼል
– ፍልውሃ ሸራተን አካባቢ መስጊድ
– ኦርማ ጋራዥ
– ንግድ ማተሚ ቤት
– ራስ መኮንን ድልድይ
– አፍንጮ በር ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።