ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– “ወቅቱ ንፋስ የቀላቀለ የአየር ሁኔታ ያለበትና ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲል የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ፣ ኮምሽኑ ድንገተኛ የእሳትም ሆነ የጎርፍ አደጋዎች ቢያጋጥሙ አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረግ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸው “ወቅቱ ደረቃማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታና ለእሳት አደጋ አጋላጭ በመሆኑ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ሊያደረግ ይገባል” ብለዋል፡፡
ህበረተሰቡ የእለት ተእለት ኑሮውን ለማከናወን ቡታጋዝ፣ ሲሊንደር እንዲም በተለያየ መንገድ ኤሌትሪክ ስለሚገለገል ለእሳት አደጋ በማያጋልጥ መልኩ የአየር ሁኔታውን ከግንዛቤ ውስጥ ባስገባ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ አያይዘው የተናገሩት አቶ ጉልላት፣ ኮምሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆኑ ጎርፍ የሚከሰትባቸውን ቦታዎች ለመለየት ጥናት እያደረገ መሆኑንና ጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች እንዳይከሰትም ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡