አሜሪካ “በኢትዮጵያ ከቀጣዩ ምርጫ በኋላ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ” ስትል ጥሪ አቀረበች!

አሜሪካ “በኢትዮጵያ ከቀጣዩ ምርጫ በኋላ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ” ስትል ጥሪ አቀረበች!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት እና መላ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያን የወደፊት አካሔድ ለመወሰን እና የአገሪቱን ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ከምርጫ በኋላ ለሚካሔድ አካታች የፖለቲካ ብሔራዊ ውይይት ቁርጠኛ እንዲሆኑ” ስትል አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች።

የጆ ባይደን አስተዳደር፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሠራተኞቹ ጥረቶች እውቅና መስጠቱንና ነገር ግን ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የሚካሔድበ ከባቢ አሳሳቢ መሆኑን በገለጸበት የትናንቱ መግለጫው፣ መጪው የኢትዮጵያ ምርጫ አሉበት ያላቸውን ፈተናዎች ዘርዝሮ ሥጋቱን የገለጸ ሲሆን “በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች በክልሎች እና ብሔሮች መካከል ያለው ልዩነት መካረር የአገሪቱን አንድነት እና የግዛት ሉዓላዊነት ያሰጋል” በማለትም ከምርጫው በኋላ መፍትሔ ሊፈለግ እንደሚገባ በማሳሰብ “ከምርጫው በኋላ ያለው ጊዜ ኢትዮጵያውያን ተባብረው እነዚህን ልዩነቶች ለመጋፈጥ ኹነኛ ወቅት ነው” ብሏል።

LEAVE A REPLY