ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ትላንት ሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም፣ አሥራት ሺካ እና ሮቤል ልደቱ የተባሉ ሁለት ወጣት ኢንጂነሮች ለሥራ ጉዳይ ወደ አማሮ ልዩ ወረዳ ሲጓዙ፣ ጀሎ በምትባል ቀበሌ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ተችሏል።
የአማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት፣ የወጣቶቹን ግድያ አረጋግጦ ጉዳዩን ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዳሳወቀ የገለጸ ሲሆን፣ የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽን ባለልስጣን በበኩሉ፣ ወጣት ሮቤል ልደቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንግስት ፕሮጀክቶች ግንባታ ጥራት ክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሂደት ባለሞያ እንደነበር ገልጾ በህልፈቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
ይሁንና የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ስለግድያውና ጥቃት ፈፃሚዎቹ ማንነት እስካሁን ያለው ነገር የለም።